Thursday, November 23, 2006

ለኢትዮጵያውያን ስደተኞች እንጩህላቸው !!
choreber (ጮሬበር)Blogger

በሱዳንና በእንግሊዝ ሃገር የፖለቲካ ጥገኝነት የሚጠይቁ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች እየተያዙ ለአምባገነኑ የመለስ ዜናዊ አገዛዝ ሊሰጡ መሆኑን ከኢንተርኔት ላይ እያነበብን ነው ። ሁላችንም እንደምናውቀው ዛሬ ፤ ኢትዮጵያ ፤ የፖለቲካ ፕሮግራማቸውን በሰላማዊ መንገድ ብቻ ሲያራምዱ የቆዩ ኢትዮጵያውያን ፤ መሳሪያ ያልታጠቁና በብዕር ብቻ ነፃ አመለካከታቸውን በነፃ ጋዜጦች ሲገልፁና ለህዝቡም ነፃ አንደበት የሁኑለት ነፃ ጋዜጠኞች ፤ የህዝቡን ሰብዓዊ መብቶች ለማስከበር በሚያደርጉት ትግል የታወቁ ግለሰቦች ፤ የመምህራን ማህበር አመራር አባሎችና መምህራን ፤ ከአንደኛ ደረጃ ት/ቤት እስከ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ፤ ነጋዴዎችና አምባገነን ሥርዓትን የሚቃወሙ ኢትዮጵያውያን በሙሉ ፤ ዘር ፤ ፃታና ህይማኖት ሳይለይ የተገደሉባት ፤ የታሰሩባትና እየተዋከቡ የሚኖሩባት ሃገር ናት ።

ኢትዮጵያ ወደ መግደያ ቻምበር እና እስር ቤት ከተለወጠች ቆየች ። መሪዎቿም የአፍሪካ የዘመኑ ናዚዎች ሆነዋል ። ከሰብዓዊ ፍጡርነት ወደ አውሬነት ራሳቸውን ከለወጡ ብዙ ጊዜያቸው ነው ። ለዚህ ሥርዓት አልባ መንግሥት ለሚመስል መንግሥት ነው ኢትዮ ጵያውያን ከየተገኙበት እየታነቁ የሚሰጡት ። ሁላችንም ራሳችን ላይ እንዲደርስ በማንፈልገው ሁኔታ ውስጥ ነው ያሉት ። እናም እንድረስላቸው !! አንብበን ዝም አንበል ። ሰምተን ዝም አንበል ። ምራቅ መምጠጥ ብቻ አይበቃም ። ብናምንም ባናምንም ለኛ ለኢትዮጵያውያን ከራሳችን ውጭ ማንም የለንም ። ማንም አይረዳንም ። ብዙ ጊዜ ብዙ ቦታ አይተናል ። የሚፈልገን እንጂ የሚረዳን የለም ። የሚፈልጉን ደግሞ ለጦርነት ብቻ ነው ። ስንሞት ደስ ይላቸዋል ። ለረሃብ ብቻ ነው የሚፈልጉን ። በረሃብ ስንቆላ ደስ ይላቸዋል ። የኛ ረሃብ ለነሱ ገንዘብ ለኛ ግን ሞት ነው ። በሞታችን ይደንሳሉ ። በሞታችን ብዙ ገንዘብ ይዝቃሉ ። የኢትዮጵያውያን ሞት ለብዙዎቹ አትራፊ ኮርፕሬሽን ነው ። ስለዚህም ለወገኖቻችን እንጩህላቸው ። ለስደተኛው ህብረተሰብ እንጩህ !! በስደት አለም እየተሰቃዩ እንዳይኖሩ እንጩህ ። የኢትዮጵያዊ ነፍስ ምኑም ላልሆነው መለስ ዜናዊ እንዳይሰጡ እንጩህ ።



No comments: