Friday, August 10, 2007

ስለ ኦጋዴን ጋዝ ከበሮ በዛሳ !!!

"የቬኑዜላ ፕሬዚዳንት ፣ ሁጎ ቻቬስ ፣ ከኢኳዶር አቻቸው ጋር 5 ቢሊዮን ዶላር ሊፈጅ ይችላል የተባለለት የነዳጅ ዘይት ማጣሪያ ስምምነት አደረጉ" በተባለበት በዚህ ሰሞን የኢትዮጵያ መንግሥት በኦጋዴን ክልል በካሉብና ሃላል ያለውን ጋዝ ለማልማትና ወደ ዓለምአቀፍ ገበያ ለማቅረብ የማሌዥያ መንግሥት ንብረት ከሆነው ፔትሮናስ ጋር የ1.9 ሚሊዮን ዶላር ስምምነት ኩአላ ላምፑር ላይ መፈራረሙ እኔን አላስደነቀኝም ። ዕድሜ ልካችንን ስንታለልበት ለከረምነው የኢትዮጵያ የነዳጅ ጉዳይ አሁንም ፣ አሁንም እየደጋገማችው ግራ አታጋቡን ። አንዲት የነዳጅ ጠብታ በዓይናችን ሳናይ በራዲዮና በቴሌቪዥን ብቻ አታደንቁሩን ። ከአሥር ዓመት በፊት ይኸው የኦጋዴን ነድጅ ሊወጣ ነውና "አክሲዮን ግቡ "ብላችው ነበር ። አዲስ ዘመን ጋዜጣ ወሬው እሱ ብቻ ነበር ።የአክሲዮኑ ነገር ደብዛው ጠፋ ። የሚያነሳውም የለም ። "ኡፈይ ! "ምርጫችን ባይሆንም "ኡፈይ ! "አልን ። ስለዚሁ የነዳጃችን ጉዳይ አንድ ጓደኛዬ "ነዳጁ ያለው ቴሌቪዥኑ ውስጥ ነው " ብሎ ከነገረኝ ቆይቷል ። አምኜዋለው ። ስለእውነት ፣ የአንዲት ሰሞን የፖለቲካ ኡኡታ ካልሆነ በቀር የ1.9 ሚሊዮን ዶላር ጋዝ የማውጣትና መስመር የመዘርጋት ስምምነት ይህን ያህል ምን ሆነና ነው ከበሮ የበዛለት? የጋዙ ማስተላለፊያ ቱቦ ወይም መስመር እውነት ኦጋደንን አቋርጦ ፣ ሞቋዲሾ ወይም ሶማሊላንድ በርበራ አልያም ጅቡቲ ወደብ ድረስ ይዘረጋል ? እሺ ፣ ስንት ጊዜ ስንት ዶላር ያስፈልገዋል ? የ1.9 ሚሊዮን ዶላር ስምምነት ለዚያ ሁሉ በቂ ነው ማለት ነው ? ወይስ የኢኮኖሚና የፖለቲካ ደረቅ ቀልድ መቀለድ ስለማያሳፍራችው ያንኑ እንጨት እንጨት የሚል የገዳይ ቀልድ እንደለመዳችውት በኛ ላይ መልቀቃችው ነው ? ? ?

ወንድሞቼ ሆይ ፤ በየትኛው ሰላም በየትኛው ምቹ የልማት ወቅት ነው ይንን ለማድረግ ቆርጣችው የተነሳችውት ? ለሃገር አሳቢና ለሃገር ልማትና ዕድገት ተቆርቋሪ ብትሆኑ ኖሮ መጀመሪያ ጋዙ ካለበት የኢትዮጵያ መሬት ላይ እንደማንኛውም ዜጋ ኢትዮጵያዊ ሆነው ከሚኖሩት የኦጋዴን ሰዎቻችን ጋር መነጋገር ነበረባችው ። የኦጋዴን ህዝብ ደግሞ ከወያኔ ይልቅ የሚያደምጠው ኦብነግን መሆኑን እኛ አናውቅ እንደሆን እንጂ እናንተ አሳምራችው ነው የምታውቁት ፤ በአጩሜው ተዠልጣችዋልና !! ደሳሳ ጎጆውን በላውንቸር ከምታጋዩበት ፣ ዕርዳታ የሚያገኝበትን መንገድ ከምትዘጉበት ፣ ሴቶቻቸውን አስገድዳችው ከምትደፍሩባቸው ፣ የልማትና የሰብአዊ ሰራተኞቻቸውን ከምትገድሉባቸው ፣ ቀይ መስቀልን ከምታስወጡባቸው ይልቅ ከኦብነግ ጋር ገለልተኛ የሆኑ አስታራቂዎች ባሉበት በሶስተኛ ሃገር ላይ ብትመካከሩ ኖሮ እናንተ ከመረጣችሁት ፍጅት የተሻለ ነገር ባየን ነበር ። ግን አልሆነም ። ምክንያቱም እናንተ አንዴ በመግደል ተወልዳችዋል ። በመግደል አድጋችዋል ። በመግደል ሸምግላችዋል ። በመግደል አፍሮ የነበራችው መንደርተኞች ዛሬ በመግደል መላጣና ሸበቶ ሆናችዋል ። ብሩህ ዓይን የነበራችው ሰዎች ዛሬ በመግደል መነጽር ለብሳችዋል ። የናንተ ግድያ መቆሚያው የትና መች እንደሆነ ማንም አያውቅም ። 17 ዓመት ጫካ ገደላችው ። 16 አመት ከተማ እየገደላችው ነው ። ጋምቤላ ትሄዳላችው - ትገድላላችው ። ኦሮሚያ ትሄዳላችው - ትገድላላችው ። አዋሳ ትሄዳላችው - ትገድላላችው ። ጎንደር ትሄዳላችው - ትገድላላችው ። ኦጋዴን ትሄዳላችው - ትገድላላችው ። ከማን ጋር ነው መኖር የምትፈልጉት ? በኢትዮጵያ ምድር ከሚገኙት አብዛኛው ብሄረሰቦች ጋር ተናክሳችው ፣ ተቧጭቃችው ፣ ሆድና ጀርባ እሳትና ጭድ ሆናችው እንዴት ነው በሥልጣን መቆየት የምትፈልጉት ? ለመሆኑ እናንተ ኢትዮጵያ ውስጥ ምን ዓይነት ሥርዓት ለማስፈን ነው የበሽታና የረሃቡን ዱካ እየተከተላችው ከበሽታና ከረሃብ የተረፈውን ሰላማዊ ሰው ከዳር እስከ ዳር የምትፈጁት ? ? ? እና ደግሞ ከሁለት ወይም ከሶስት አልያም ከስድስት ወራት በኋላ ማነው በናንተ ጥይት የሚረፈረፈው ባለተራ ብሄረሰብ ? እሱን እያሰብኩ ነው የምጽፈው ። የግድያ ልክፍታችው ከገዛ ሃገራችን ድንበር ተሻግሮ የሰው ሃገር ድረስ መዝለቁ የታወቀ ነውና የናንተ መድፍ የሚረጭበት የሚቀጥለው ባለተራ ሃገርስ ማን ይሆን ? ? ?

ባለመድፍ ወንድሞቼ ፤ ከላይ ለጠየኳችው ጥያቄዎች ከቻላችው መልሱን ስጡኝ እንጂ የኦጋዴንን ህዝብ መግደላችውን በመገናኛ ብዙሃን ባስነገራችው ማግሥት ስለጋዝ አታውሩልን ። በ1.9 ሚሊዮን ዶላር የግለሰብ ሃብት የሆነ አነስተኛ አጂፕ የነዳጅ ማደያ እንጂ በሃገር ደረጃ የሃገር ሁሉ ከበሮ የሚደለቅለት የጋዝ ልማት ሰምቼም አላውቅም ። አንድ ቀን ለማደር ብላችው የማይሆን ዝባ ዝንኬ በመገናኛ ብዙሃን እየለቀቃችው ሚዲያውን አታርክሱት ። የአየር ጊዜውን አትጫወቱበት ። የቬኑዜላ ህዝብ ስለ 5ቢሊዮን ዶላር የነዳጅ ማጣሪያ ያወራል ፤እናንተ ገዳዮች ፈርዶባችው ስለ 1.9 ሚሊዮን ዶላር ጋዝ ወሬ ትለፈልፋላችው ። ማፈሪያዎች !!!

Wednesday, July 18, 2007

ወያኔዎች ፤ መግደልና ማሰር አይሰለቻችሁም ወይ?
አሥራ ስድስት አመት ሙሉ ገደላችው ። አስራችው ። አሰደዳችው ። የቻላችሁትን ያህል ገንዘብ ዘረፋችው ። ጫካ ውስጥ የረባ ምሽግ እንኳ ያልነበራችው ፍጡሮች ዛሬ ቤተመንግስት የመሳሰለ መኖሪያ ቀልሳችው ትኖሩበታላችው ፤ የተረፋችሁንም ለፈረንጅ ታከራያላችው ። በኢትዮጵያ ምድር ሁሉም ነገር የናንተ ሆኗል ። የናንተ እጅና እግር የሌለበት ወይም ያልደረሰበት የንግድም ሆነ የልማት ተቋም የለም ። የኢትዮጵያን የልጅ ልጆች ሁሉ በዱቤ ቸብችባችው ዶላሩን ወስዳችሁታል ። በውጭ ያሉ ባንኮች ለዚህ ምስክር የሚሆኑበት ጊዜ ሩቅ አይሆንም ። ከአሁን በኋላ የሚወለዱ ኢትዮጵያዊ ህፃናት ከናታቸው ማህጸን ሲወጡ በአንገታቸው የዱቤ ሠርተፊኬት አንጠልጥለው መሆኑን ካወቅን ቆይተናል ። ወባን "አይዞህ በርታ" ብላችው አዲስ አበባ የጨመራችው ጥቂት ማፍያ ሠዎች ይህ ሁሉ የናንተ ሆኖ ሰላማዊውን ዜጋ ትገድላላችው ፤ ታስራላችው ፤ ታሰቃያላችው ። ምን አድርግ ፣ ምን ሁን ነው የምትሉት ? እሽ ምን እንሁን ? ....... ንገሩን እንጂ !!!እንዴት አንድ "ጭቆና አንገፈገፈኝ!" ብሎ ጫካ ውስጥ መከራውን የበላ ፤ የተናቀና የተዋረደ ቡድን በለስ ቀንቶት መንግሥት የመሆን እድል ሲገጥመው ተመልሶ ጨቋኝ ይሆናል ? ያውም የከፋ ! ኢትዮጵያ በታሪኳ አይታው የማታውቀው ጨቋኝና ውሸታም መንግሥት !! .....ለጋዜጠኛ የእድሜ ልክ ፍርድ የሚሰጥ መንግሥት !! ..... ሰላማዊ እንደሚሆን በተነገራቸው የምርጫ ሂደት ላይ የተሳተፉ ምሁርና ሽማግሌ ባለራእይ ዜጎችን የእድሜ ልክ እስር የሚሸልም እርጉምና በራሱ የማይተማመን መንግሥት - ያውም አሸንፈውት ። ለምረጡኝ ዘመቻ የተጠቀሙበትን የቅስቀሳ ንግግር ለመክሰስ የተጠቀመ ፤ ከዚያም የእድሜ ልክ እስራት የበየነ ዓይን አውጣ መንግሥት !! ጠመንጃችው ከጀርባቸው ዞር ቢል ባዶ ሆናችው የምቀሩ እናንተ የገዳይ ማህበር አባላት እባካችው ህዝቡን እስቲ ምን አድርግ ፣ ምን ሁን ነው የምትሉት ? እሽ ምን እንሁን ? ...... ንገሩን እንጂ !!!በምርጫው ሰበብ ያሰራችኋቸውን አሸናፊ ተመራጮች አንገታችሁን ተይዛችው መፍታታችው ላይቀር ለምንድ ነው ሁለት አመት ሙሉ ያሰቃያችዋቸው ? የህግ ሥርዓታችሁ የበሰበሰና የገማ መሆኑን ማንም ነው የሚያውቀው ። በሱ መነገድ እንደሆን አይቻልም ። ይሄ የሰለጠኑና ሰርቲፋይድ የሆኑ ምስክሮችን ከየትም እየለቃቀመ "በምስክር ስም" ለችሎት የሚያሰማ ፍርድ ቤት የናንተ አንዱ የማጥቂያ ብርጌድ ነው እንጂ ፍርድ ቤት አይደለም ። ለምን "መብረቅ" ወይም "በርቂ" ወይም " ክብሪት ብርጌድ" ወይም "ሬጅሜንት" አትሉትም !! እንደዚያ ብትሉት ነበር የዓለም ህብረተሰብ የሚያምናችው ። ለዚያው ሰርቲፋይድ ምስክሮቹ ሰርቲፋይድ ያልሆኑበትን የእውነት ቃል ሲለፈልፉ እየተሰማ ። እነዚህን ሰዎች ለመፍታት ሺ ስም ብትሰጡ "ምህረት" ፣ "ይቅርታ ጠየቁ" ፣ "ስህተታቸውን አመኑ " ፣ ግማሽ ሃላፊነት ወሰዱ" ብትሉ ፤ የፈለጋችሁትን ቃላት ብትደረድሩ አምኖ የሚያዳምጣችው የለም ። ሰዎቹ የሚፈቱት አንገታችሁን ስለተያዛችሁ ብቻ መሆኑን ነው የምናውቀው ። የታሰሩትም ስላሸነፏችው ነው - ያውም በዝረራ ! በባዶ ! በዜሮ ! ታንክ ሳይኖራቸው...... ይህን እወቁ ። ማንም አይረሳም ። ከማንም ኢትዮጵያዊ ህሊና ውስጥ የሚፋቅ ታሪክ አይደለም ። የሚፈቱትም ስላሸነፏችሁ ነው - ታንክ ሳይተኩሱ ። እነሱን እስር ቤትአጉራችው እናንተም እኛም እንቅልፍ የለንም ። ኢትዮጵያዊው በሙሉ አይተኛም ። አልተኛም ። ይህን ታውቃላችው ። ከምርጫው በፊት የነበረው አተኛኘታችውና አተኛኘታችን ከምርጫው በኋላ ተለዋውጧል ። ግን ግን እኔ የማይገባኝ መግደል የምታቆሙት መች ነው ? ማሰርስ ? እንደናንተ ማሰርና መግደል የሚወድ የለምና !!አንድ ነገር ልንገራችው ። አዲስ ነገር አይደለም የምነግራችው ። 16 አመት ሙሉ የኢትዮጵያ ህዝብ የነገራችውን ነው የምነግራችው ። መንገር ሳይሆን ማስታወስ ልበለው መሰል ። ሰላማዊ ሰዉን በየአስፋልትና ገጠር ላይ ስለደፋችሁት ፤ ጨለማ ቤት ስላጎራችሁት ፤ እንደለመዳችሁት 40 ሺ ወጣት ሰብስባችው ስለቀጠቀጣችው ወይም ስላሰራችው ፤ እድሜ ልክ ወይም 20ና 30 አመት ስለፈረዳችው ፤ የኢትዮጵያዊው የለውጥ ስሜት ፣ ጉጉት ፣ የመናገር ፣ የመሰብሰብ ፣ በፈለገው የሙያም ይሁን የፖለቲካ ማህበር የመደራጀት ፣ በመረጠው የፖለቲካ ሥርዓት ጎዳና መጓዝና ከልቡ በመረጠው ተመራጭ መተዳደር ተስፋው አይሞትም ። ምንም ተባለ ምን የጊዜ ጉዳይ ካልሆነ በቀር ይኸው ይፍፈጸማል ። የሠው ልጅ የለውጥ ስሜት በመግደል አንድ ቦታ አይቆምም ። ለውጥን በማሠር ማገድ አይቻልም ። ለውጥ ሂደት ነው ። ይሄዳል ። የኢትኦጵ መጽሄትና ጋዜጣ አሳታሚ ድርጅት ባለቤት የሆነውን ጋዜጠኛና አሳታሚ ሲሳይ አጌናን ወደ 100 ሺ የሚገመት ጥሬ ገንዘብ "ለምርመራ" በሚል ሰበብ ቀምቶ ዛሬ ደግሞ 100ሺ ብር እንዲከፍል ፍርድ ቤቱ መፍረዱ ምንድ ነው የሚባለው ? ። የፈለገ ዓይነት የጭካኔ ፍርድ ከፍርድ ቤቶቹ ብርጌድ ቢተኮስ ለውጥ ኢትዮጵያ ውስጥ አይቀርም ። እናንተ ምን እንደምትሉን ባይገባኝም እኔ በበኩሌ እንዲገባችሁ አድርጌ የምለው አለኝ - " እያንዳንችሁ የእጃችሁን ታፍሳላችው ..... በንጹሃን ደም የበሰበሰው እጃችሁና በዘረፋና በትዕቢት ያበጠው ልባችው አንድ ቀን ፍርዱን ከኢትዮጵያ ህዝብ ያገኛል ። በመንግሥትነት ስም በቡድን ተደራጅተው የኢትዮጵያን ህዝብ የገደሉ ሁሉ ሲዋረዱ አይተናል ። እናንተም ከዚያ ውርደት አታመልጡም ።

በመጨረሻም ..... ምን አድርግ ፣ ምን ሁን ነው የምትሉት ? እሽ ምን እንሁን ? ..... ንገሩን እንጂ ! መደብደብ ፣ ማሰር ፣ መግደል ፣ በቶርቸር ማሰቃየት ፣ ማሰደድ ፣ ባንክ ዘራፊ ሆናችው "ባንክ ዘራፊ ነው .... የሰለጠነ አድማ በታኝ ፖሊስ እና ውኋ መርጪያ የለንም" ማለት አይሰለቻችሁም ። ስንት መሬት ፣ ስንት ሰላማዊ ሰውና ስንት ብር ነው መብላት የምትፈልጉት ? ? ? ? ? ጅቦች !! የሠው ጅቦች !!!!


Thursday, May 17, 2007
IPI resolutions on Ethiopia journalists held in prison.

Meeting at its Annual General Assembly 14 May, 2007 in Istanbul, Turkey, the IPI members,International Press Institute, adopted a resolution calling on the Ethiopian authorities to immediately release all imprisoned journalists and refrain from punishing the media for its reporting.

The IPI membership believes that editors and journalists have been arrested as a punishment for their writing. Therefore, the IPI membership calls on the Ethiopian government to release all imprisoned journalists, halt the closer of media organizations and allow the foreign media access to the country. (to read full text please go to ''www.freemedia.at'')

Thursday, May 03, 2007
Journalists held in Ethiopia's jail should be released.
ወሬ አታብዙ ጋዜጠኞችን ፍቱ ፤
ኤሊያስንም ለቀቅ አድርጉት
Ethiopia, where the government launched a massive crack down on the private press by shutting newspapers and jailing editors,leading CPJ's (Committee to Protect Journalists), dishonor roll.
Indicator: Imprisonments rise from two to 18. Dozen forced into exile.In 2006 alone,authorities ban eight newspapers,expel two foreign reporters, and block critical Web sites.Only a handful of private newspapers now publish, all under intense self-censorship.
Committee to Protect Journalists,CPJ.
Ethiopia has acquitted 8 newspaper editors and publishers but still holds at least 12 more that were rounded by following the aftermath of the 2005 general elections. All the prisoners were accused of attempted genocide and treason and faced life imprisonment or death penalty if convicted.
International Federation of Journalists,IFJ.
Freedom House has tracked a disturbing five-year downward trend in Ethiopia,where an already repressive environment became much worse in 2006 since the government began cracking down on critical journalists be expelling foreign correspondent and imprisoning opposition reporters.
Freedom House
Internet watchdog on Thursday accused Ethiopia of blocking scores of anti-government Web sites and millions of blogs in one of sub-Saharan Africa's biggest cases of cyber-censorship.Woyanne propaganda minister dismissed the report as "a baseless allegation." "We may have technical problem from time to time ,"information minister spokesman Zemedkun Tekle. "But we have not done anything like that." Liar!
The OpenNet Initiative- a partnership between Harvard law School, and University of Toronto and Cambridge and Oxford-said it had gathered proof of interference. "We have run diagnostic tests using volunteers in Ethiopia which indicate that they are blocking IP addresses," OpenNet research director Robert Fan's said, referring to the unique numeric addresses of Web sites---
Ethiopian Review

ማስታወሻ ከጮሬበር
ኤሊያስ ክፍሌን በመክሰስ ብቻ ጊዜያችሁን አታጥፉ ። አንዴ ሃገር ውስጥ ፣ አንዴ በውጭ ሃገር....። በፍፁም አልቻላችሁትም ። ግፋ ቢል በሁለት አሮጌ ኮምፒውተሮች ነው መከራ የሚያሳችው ። እናንተ ግን ብዙ ብሮችና ብዙ የተባበረ ጭንቅላት ይዛችው ነው የምትከታተሉት ። ያውም በመክሰስ ጭምር ። የመሰላችሁን ትፅፉ የለም እንዴ ስለኤሊያስና ድረ ገፁ !! ኤሊያስ መች ከሰሳችው !! ፀሃፊ ነን የምትሉ ከሆነ ብዕራችውን አሳዩን እንጂ ሃምሳ ጊዜ ፍርድ ቤት አትሩጡ ። ኤሊያስ እኮ ስሙንና አድራሻውን በግልፅ አስቀምጦ ነው የሚፅፈው ። ሁልጊዜ እሱን የምትወነጅሉት ሰዎች የት ነው ያላችሁት ? እነማን ናችው ? "ወያኔ ናችው" ከመባል በቀር ምንም መረጃ የለንም ። ወያኔ ደግሞ አንድ ሰው ወይም መለስ ዜናዊ ብቻ ዓይደለም ። ህዝቡ የመለስ አስተዳደርን "ሰላማዊ ሰው ገዳይ ነው" ብሎ ለለውጥ የተነሳሳው ሌላ ገዳይ ለመተካትም አይደለም ። መንግሥትና የመንግሥት ደጋፊዎች እንደምትሉት "ሕገ-መንግሥታዊውን ሥርዓት ሕገ-መንግሥታዊ ባልሆነ አካሄድ" ለመገልበጥ የሞከረም የለም ። ይህ ሁሉ ውሸት መሆኑን ታውቃላችው ። እንደኔ ፣ እንደኔ እባካችው ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ መብቱን በሚገባ የሚጠቀመውን አንድ ኤሊያስ ክፍሌና ድረ ገፁን አትዘንጥሉ ። ይህን ጋዜጠኛ ኢትዮጵያ ውስጥ ብታገኙት እኮ በመድፍም የምትለቁት አይመስልም - እንደ አፈራራችው ።

Thursday, April 19, 2007

Virginia-Tech, a shocking massacre.
Washington D.C. metropolitan area is a center for Ethiopian origin citizens. I used to live in Virginia and I knew so many Ethiopian origin students who have been going to Virginia,DC or Maryland Universities for their higher education program. I have shocked when I heard news about the killings of students, professors and staff members at Virginia Tech.I know it is tough for families, friends and communities who lost their loved ones.For me it is a nightmare and an unacceptable on this bright century, and an educational institutions should be out of gun.

Tuesday, April 17, 2007

More Cruelty of Government.
For some of us who born or grew up in civilized and rich country, situation of human rights in Ethiopia has been not as we expected.Everyday when we are trying to see some thing positive about our country's current situation from the international media outlets, unfortunately, we have been colliding with killing or jailing words. Today, I have read an article of cruelty of Ethiopian government in Western Ethiopia from the Sanfrancisco Chronicle, page A-8.
To read full story, Source: The Sanfrancisco Chronicle, Link: ER

Monday, April 16, 2007

Report of torture in Ethiopia are wide spread
For those who believes the principle of democracy but don't want to read about shocking stories of Ethiopian innocent citizens - killed or tortured - by Ethiopian government, please, read the Sanfrancisco Chronicle report to update your information.

Ghimbi-Ethiopia :
First,the police officer threw Tesfaye in to a dark cell. Then, each day for 17 days it was the same routine: Electric shocks on his legs and back, followed by beatings with rubber truncheons. Four or five officers would then surrounded and kick him. At last, a large bottle of water would be tied around his testicles. He'd pass out. (Read full report)